Hagerigna

Song

Hagerigna

Sami Dan · Asira Andu Getsoche · 2019 · 5:24

Lyrics

የዚህ ዘመን ሰው ነኝ እዚች ምድር ምኖር ከሰው ዘር መገኛ ሆኜ ነፀብራቋ ማንነቴ ሁሉ ሀገርኛ ሀገርኛ ሀገርኛ ሁሉም ባገርኛ ሀገርኛ ሀገርኛ ሁሉም ባገርኛ አለም ተከፋፍላ ሁሉም በያገሩ ከነባህላቸው ባሉበት ሲኖሩ እኔም አንዱ ሆኜ ከነማንነቴ የሌላን ሳልነካ ኖርኩኝ እንደ ቤቴ ሀ ሀ ሀ ሀ ከነነፃነቴ ሀ ሀ ሀ ሀ ባህሌ ውበቴ ስጨፍር ስዝናና ሁሉም ባገርኛ ስጣላም ስታረቅ ሁሉም ባገርኛ ሰላምታዬም አክብሮቴም ሁሉም ባገርኛ ሀገርኛ ሀገርኛ ሁሉም ባገርኛ የሀገሬ ሰው በቅኝ ያልተገዛ አለው ብዙ ታሪክ ከአፈሩ የበዛ ተጣልተው ማይችሉት በፍቅር የሚያስሩት ከነሱ አንዱ ነኝ ሀበሽ የተባልኩት ሀ ሀ ሀ ሀ ቀርበው የማይርቁት ሀ ሀ ሀ ሀ ሁልጊዜም የሚያምኑት ጋብቻዬም አይ ለቅሶዬም ሁሉም ባገርኛ የማጌጠው የምለብሰው ሁሉም ባገርኛ ፉከራዬም ሽለላዬም ሁሉም ባገርኛ ሀገርኛ ሀገርኛ ሁሉም ባገርኛ (Oromiffa) ፊደሉም የኔው ነው ቋንቋውም የራሴ ከኔ ጋራ አድጓል ተጣብቆ ከነፍሴ ማሙሽና ሚሚ አለ ሚጫወቱት ከእናት ከአባታቸው ከአያት የወረሱት ሀ ሀ ሀ ሀ ሁሌም የማይረሱት ሀ ሀ ሀ ሀ አድገው ሚናፍቁት ኩኩሉ ፣ አባሮሽ ሁሉም ባገርኛ እቴ ሜቴ ፣ በዛ በበጋ ሁሉም ባገርኛ ሆያሆዬ ፣ አበባይሆሽ ሁሉም ባገርኛ ሀገርኛ ሀገርኛ ሁሉም ባገርኛ ሀገርኛ ሀገርኛ

Lyrics provided by LRCLIB.

Popular by Sami Dan